Fana: At a Speed of Life!

አርመኒያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት ይበልጥ እንደምታጠናክር ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አርመኒያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን በወዳጅነት ላይ የተመሰረተ ግንኙነት አጠናክራ እንደምታስቀጥል አስታውቃለች፡፡

በኢትዮጵያ የአርመኒያ አምባሳደር ሳህክ ሳርጊሲያን የመቻል ስፖርት ክለብን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ ስለመቻል ስፖርት ክለብ ታሪካዊ አመጣጥ፣ ስለ ክለቡ ስፖርተኞች የኦሊምፒክ ተሳትፎ፣ ስለ ክለቡ አሁናዊ አወቃቀርና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ለአምባሳደሩ ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡

የመቻል ስፖርት ክለብን ሙዚዬምና ዘመናዊ ጅምናዚዬም መጎብኘታቸውንም የመከላከያ ሰራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ መረጃ ያመላክታል፡፡

አምባሳደር ሳሀክ ሳርጊሲያን ኢትዮጵያና አርመኒያ ታሪካዊና ጠንካራ ግንኙነት እንዳላቸው አስታውሰው፤ በቀጣይ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን በወዳጅነት ላይ የተመሰረተ ግንኙነት የበለጠ አጠናክረን ለማስቀጠል በተለያዩ መስኮች ዙሪያ እየሰራን ብለዋል።

አርመኒያ ወታደራዊ ስፖርት ክለብ እንዳላት ጠቁመው÷ ክለቡን መጎብኘታቸው ተሞክሮ ለመለዋወጥና በቀጣይ በስፖርቱ ዘርፍ በትብብር ለመስራት ያግዛል ሲሉ ተናግረዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.