Fana: At a Speed of Life!

አብርሃም በላይ (ዶ/ር) ከዩ ኤስ ኤይድ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (ዩ ኤስ ኤይድ) የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ስኮት ሆክላንደር ከተመራ ልዑክ ጋር ተወያዩ፡፡

ውይይታቸው በጥር ወር 2016 ዓ.ም ይፋ የተደረገውና በቆላማ አካባቢዎች የሚተገበሩ ፕሮጀክቶች ለተጽእኖ የማይበገሩ የማድረግ አላማ ያለው ‘Partnership for Lowlands Resilience Activity’ ፕሮጀክት አፈጻጸም ላይ ያተኮረ ነው፡፡

ለሦስት ዓመት ለሚተገበረው ፕሮጀክት የሚያስፈልገውን የ3 ሚሊየን ዶላር ወጪም ዩ ኤስ ኤይድ መሸፈኑን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

ፕሮጀክቱ በሶማሌ፣ አፋር፣ ኦሮሚያ እና ደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች የሚገኙ አርብቶ አደሮችን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑም ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.