Fana: At a Speed of Life!

በፍራንኮ ቫሉታ በቂ ምርት ወደ ሀገር ውስጥ እየገባ መሆኑ ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቂ ምግብ ነክ የምርት አቅርቦት እንዲኖር የሚያስችል የባለድርሻ አካላት ውይይት መደረጉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ሚኒስትሩ ምግብ ነክ የምርት አቅርቦትን በተመለከተ ከብሄራዊ ባንክና ከጉምሩክ ኮሚሽን አመራሮች ጋር መምከራቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

በውይይቱ በመንግስት እንዲሁም በግል አስመጪዎች በኤልሲና በፍራንኮ ቫሉታ መንገድ ምን ያህል ምግብ ነክ ምርቶች ወደ ሀገር ውስጥ እየገቡ እንደሆነና የወደፊት አቅርቦት ምን ሊመስል እንደሚችል ገምግመናል ብለዋል፡፡

በዚህ መሰረትም መጠኑ ከፍተኛ የሆነ ምርት በፍራንኮ ቫሉታ መንገድ ወደ ሀገር ቤት እየገባ መሆኑን እና ይህም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነጻጸር በእጥፍ እንደሚበልጥ ጠቅሰዋል፡፡

ስለሆነም የግብይት ማዕከላት በቂ ምርት እያገኙ መሆኑን ጠቁመው÷ይህንኑ አጠናክሮ ለማስቀጠል በተቋማቱ መካከል ተመሳሳይ ግንዛቤና አተገባበር ሊኖር እንደሚገባ መግባባት ላይ መደረሱን ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪም የጋራ መረጃ እንዲኖራቸው እና አቅርቦቱ በተረጋጋ ሁኔታ እንዲቀጥል ለማድረግ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ስምምነት ላይ መደረሱን አስገንዝበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.