3ኛው የሳይበር ታለንት ሰመር ካምፕ መርሐ ግብር ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር 3ኛውን የሳይበር ደህንነት የሰመር ካምፕ መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት አስጀምሯል።
የአስተዳደሩ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ÷በፕሮግራሙ ከመላው የኢትዮጵያ ክፍል የተወጣጡ 300 ታዳጊ ወጣቶች መሳተፋቸውን ተናግረዋል፡፡
የዲጂታል እድገት ይዞት የመጣውን ዕድል ለሀገር ልማትና ዕድገት ለማዋል በሳይበር ደህንነት ዘርፍ ልዩ ተሰጥኦ ያላቸውን ታዳጊ ወጣቶች መለየትና ማብቃት ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በዚህ ረገድ ኢመደአ ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ የሳይበር ታለንት የሰመር ካምፕ ፕሮግራም በየዓመቱ በማዘጋጀት ሥልጠናዎችን እየሰጠ መሆኑን አስታውሰዋል።
የዘንድሮው የሰመር ካምፕ ፕሮግራም ካለፉት ሁለት ዓመታት ከተዘጋጁትበቁጥርም ሆነ በተደራሽነት የተሻለ እንደሆኑ መጥቀሳቸውንም የአስተዳዳሩ መረጃ ያመላክታል፡፡