በጎፋ ዞን ለተጎዱ ወገኖችና ለአቅመ ደካማ ቤተሰብ ተማሪዎች ከ13 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ተደረገ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ በጎፋ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች፣ ለአቅመ ደካማ ቤተሰብ ተማሪዎች እና ለቤት ዕድሳት የሚውል ከ13 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ፡፡
ድጋፉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ጥላሁን ከበደ አስረክበዋል፡፡
በዚሁ ወቅትም በጥሬ ገንዘብ እና በአይነት ከተደረገው ድጋፍ በተጨማሪ ቃል የተገባ መኖሩን ሚኒስትር ዴዔታዋ ገልጸዋል፡፡
የተቋማቱ አመራሮች እና ሠራተኞች በአርባ ምንጭ እና ወላይታ ሶዶ ከተሞች የአረንጓዴ ዐሻራቸውን አኑረዋል፡፡
በታሪክነሽ ሴታ