Fana: At a Speed of Life!

በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ እስካሁን 594 ሚሊየን ችግኝ መተከሉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ- ግብር እስካሁን ድረስ 594 ሚሊየን ችግኝ መተከሉን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።

በአረንጓዴ አሻራ የአንድ ጀምበር 600 ሚሊየን ችግኞችን የመትከል መርሐ ግብር በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች እየተካሄደ ይገኛል።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴዔታ ሰላማዊት ካሳ÷ በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር እስካሁን ድረስ 594 ሚሊየን ችግኝ መተከሉን ገልጸዋል።

በመርሐ ግብሩ በ8 ሺህ 454 የችግኝ ጣቢያዎች 28 ሚሊየን የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች መሳተፋቸውን ነው የገለጹት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.