Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ጋቦን በድንበር ተሻጋሪ ወንጀል መከላከል ላይ በትብብር ለመስራት መከሩ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ከጋቦን የብሔራዊ ደህንነት ም/ቤት ዋና ጸሐፊ እና የአፍሪካ የመረጃና ደህንነት ኮሚቴ ሊቀመንበር ብ/ጄ ኢቲየን ማዳማ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም÷ኢትዮጵያና ጋቦን በድንበር ተሻጋሪ ወንጀል መከላከል፣ በመረጃ ልውውጥና በአቅም ግንባታ ዘርፍ በትብብር መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል÷ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከአፍሪካ የመረጃና ደህንት ኮሚቴ ተቋም ጋር ጠንካራ ግንኙነት ያለው መሆኑን አንስተዋል፡፡

ብ/ጄ ኢቲየን ማዳማ በበኩላቸው÷በአቅም ግንባታ ዙሪያ ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ጋር በትብብር ለመስራት ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

ሁለቱ ወገኖች ጥያቄውን ተግባራዊ ለማድረግ የመግባቢያ ስምምነት ለመፈራረም መስማማታቸውንም የፌዴራል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡

ብርጋዴር ጄኔራል ኢቲየን ማዳማ ሞሁንዲ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የታጠቃቸውን ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ተዘዋውረው መጎብኘታቸውም ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.