Fana: At a Speed of Life!

ሚኒስቴሩ ለጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታ የሚያግዙ አበረታች ተግባራትን ማከናወኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 7ኛው ሀገር አቀፍ የሰላምና ፀጥታ የምክክር መድረክ በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዷለም እንዳሉት÷ሚኒስቴሩ በበጀት ዓመቱ ከሰላምና ፀጥታ ተቋማት ጋር በመቀናጀት ለጠንካራ ሀገረ-መንግሥት ግንባታ የሚያግዙ ሀገራዊ እሴቶችን ባስጠበቀ መልኩ በተከናወኑ ስራዎች አበረታች ውጤት ተመዝግቧል፡፡

የሀገረ መንግሥት ግንባታ ከሰላም ግንባታ ተነጥሎ የማይታይ ተግባር መሆኑን ጠቁመው÷ በዚህ ላይ ዘርፈ ብዙ ተግባር ሲከናወን መቆየቱን አስረድተዋል።

ለስኬታማነቱም ከትምህርት፣ ከሃይማኖት፣ ከመገናኛ ብዙሃንና ከሌሎች አጋር ተቋማት ጋር በመቀናጀት ሰላምን ለማስጠበቅና ለማረጋገጥ በሚያግዙ ጉዳዮች ላይ ሲሰራ መቆየቱን አብራርተዋል።

ክልሎች ዘላቂና አዎንታዊ ሰላም ለማምጣት የጋራ ፎረም በማቋቋም በቅንጅት እንዲሰሩ መደረጉንና ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን ገልፀዋል።

በ2017 በጀት ዓመት በዘርፉ ተጨባጭ ውጤት በማምጣት በሀገሪቷ ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ መጠቆማቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊ አቶ ተመስገን ካሳ በበኩላቸው÷ በክልሉ ከምስረታው ማግስት ጀምሮ ለሰላም ቅድሚያ በመስጠት በተሰሩ ሥራዎች ውጤት መገኘቱን አብራርተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.