ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያውያን የኪነ ጥበብ ባለሞያዎች የአረንጓዴ ዐሻራ ቪዲዮዎችን አዘጋጅተው በማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን እንዲያጋሩ ጥሪ አቀረቡ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በፊልም፣ በግራፊክ ሥነ ጥበብ፣ በፎቶግራፍ፣ በሥነ ጽሑፍ፣ በካርቱን ሥዕል እንዲሁም በልዩ ልዩ ዘርፎች የተሠማሩ ኢትዮጵያውያን የኪነ ጥበብ ባለሞያዎች አነቃቂ የአረንጓዴ ዐሻራ ቪዲዮዎችን ቪዲዮዎችን አዘጋጅተው በማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን እንዲያጋሩ ጥሪ አቀረቡ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቴሌግራም ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ የዚህ ዓመት የአረንጓዴ ዐሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ከተጀመረ ሁለት ወር ሊሞላው መሆኑን አንስተዋል፡፡
በዚህም ኢትዮጵያውያን የኪነ ጥበብ ባለሞያዎች አነቃቂ የአረንጓዴ ዐሻራ ቪዲዮዎችን አዘጋጅተው በማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን እንዲያጋሩ ጥሪ አቅርበው÷ ለተመረጡት የሥራ ባለቤቶችም የተለየ ሽልማት ተጀጋጅቷል ብለዋል ፡፡
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።