ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በአረብኛ ቋንቋ በድረገፅና በማህበራዊ ሚዲያዎች ስርጭት ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በኦንላይን ሚዲያ በተለያዩ ቋንቋዎች ተደራሽነቱን በማስፋት አሁን ላይ በአረብኛ ቋንቋ በድረገፅ እና በማህበራዊ ሚዲያዎች ስርጭቱን ጀመረ።
ተቋሙ ቀደም ሲል በአማርኛ፣ ኦሮሚኛ፣ ትግረኛ፣ ሶማሊኛ፣ አፋርኛ እና ኢንግሊዘኛ ቋንቋዎች በተለያዩ የዲጂታል ሚዲያ ቅርፆች ይዘቶችን በማሰራጨት በየዕለቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎችን በሀገር ውስጥ ብሎም በዓለም ዙሪያ በመድረስ ላይ ይገኛል።
በአሁኑ ወቅት በተለይም በአረብኛ ቋንቋ ይዘት አቅርቦት ላይ በሀገር ውስጥ ያልውን ክፍተት በመሙላት ኢትዮጵያን በአረቡ ዓለም እና በአረብኛ ተናጋሪ ህብረተሰብ ዘንድ ለማስተዋወቅ ስርጭቱን መጀመሩን አስታውቋል።
ይህም በተለይም በመካከለኛው ምስራቅ እና በሰሜን አፍሪካ ስለ ኢትዮጵያ ለማሳወቅ የበኩሉን አስተዋፀኦ ያበረክታል ብሎ እንደሚያምንም ነው ያመለከተው።
ይህን ስራ በማስፋትም በቅርቡ በቴሌቪዥን ስርጭቱም ለአረብኛ ቋንቋ ሰዓት በመመደብ የዜና እና ፕሮግራም ይዘቶችን ማሰራጨት ለመጀመር በዝግጅት ላይ መሆኑን አስታውቋል።
https://www.facebook.com/FBC-%D8%B9%D8%B1%D8%A8%D9%89-107284611041492/?modal=admin_todo_tour