በኢትዮጵያ በ24 ሰዓታት 145 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው፤ የ5 ሰዎች ህይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5 ሺህ 552 የላብራቶሪ ምርመራ 145 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
ይህንን ተከትሎም በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 5 ሺህ 570 መድረሱን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ዛሬ ባወጡት ሪፖርት አመላክተዋል።
ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 8 ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን 2 ናሙናዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።
ከዚህ ባለፈ 3 በህክምና ማዕከል ውስጥ በህክምና ላይ የነበሩ ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን፥ በትናንትናው እለት በድምሩ የ5 ሰዎች ህይወት አልፏል።
በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 94 መድረሱን ገልፀዋል።
በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት 327 ሰዎች (317 ከአዲስ አበባ፣ 8 ከአማራ ክልል፣ 1 ከትግራይ ክልል እና 1 ከኦሮሚያ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 2 ሺህ 015 ደርሷልም ብለዋል።
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።