Fana: At a Speed of Life!

ተጨማሪ 54 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ5 ሰዎች ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰአታት ለ1 ሺህ 742 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 54 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

አሁን ላይም በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 6 ሺህ 217 ደርሷል።

የጤና ሚኒስቴር የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ዶክተር ተገኔ ረጋሳ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት በ24 ሰዓቱ በቫይረሱ ምክንያት የ5 ሰዎች ህይወት አልፏል።

በዚህም በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ሳቢያ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 114 ደርሷል ብለዋል።

በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 164 ሰዎች ከቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን በሃገሪቱ በአጠቃላይ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 2 ሺ 838 መድረሱንም ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅትም 28 ሰዎች በጽኑ ህሙማን ክፍል ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛልም ነው ያሉት።

እስካሁን በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ለ258 ሺህ 390 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ መደረጉን ዶክተር ተገኔ ረጋሰ ገልጸዋል።

በበላይ ተስፋዬ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.