ብጥብጥና ግጭቶች የተጠረጠሩ ከ4 ሺህ 700 በላይ ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየተጣራ እንደሚገኝ ተገለፀ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ብጥብጥና ግጭቶች የተጠረጠሩ ከ4 ሺህ 700 በላይ ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየተጣራ እንደሚገኝ የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክረታሪያት ሃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ገለጹ።
በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየተጣራ ያሉት ግለሰቦች በአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያና ተከትለው በተከሰቱ ብጥብጥና ግጭቶች እጃቸው አለበት ተብለው የተጠረጠሩ መሆናቸውንም አስታውቀዋል።
እነዚህ አካላት ብጥብጥ ከመፍጠር እቅድ ጀምሮ በተለያየ ደረጃ የተሳተፉ ለበርካታ ህይወት ማለፍና ንብረት ውድመት ተጠያቂ የሆኑ ናቸውም ብለዋል።
ይህንን ጥፋት በማያዳግም መልኩ ለመፍታት መንግስት ቁርጠኛ ሆኖ እየሰራ እንደሚገኝ ነው አቶ ንጉሱ ጥላሁን ያስታወቁት።
ለዚህ ሴራ መነሻ የሆነው ቡድን አሁንም በሃሰተኛ መረጃ ሽብር በመንዛት ላይ በመሆኑ ህብረተሰቡም ጥንቃቄ እንዲያደርግም አሳስበዋል።
እንዲሁም ህገ ወጦችን ለመከላከል ከመንግስት ጋር የጀመረውን ትብብር አጠናክሮ በመቀጠል ተሳትፎውን እንዲያድግ ጥሪ አቅርበዋል።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።