Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ የመሬት ፍትህ አመላካች ሰነድ ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ፍትህ ሚኒስቴር ከሄግ ኢኖቬሽን የህግ ተቋም ጋር በመተባበር ከመሬት ጋር የተያያዙ ግጭቶችን ለመፍታት የሚያስችል ልምድና ተሞክሮን የያዘ የኢትዮጵያ የመሬት ፍትህ አመላካች ሰነድ ተዘጋጅቶ ዛሬ ተመርቋል፡፡

በምረቃ ስነ ስርዓቱ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ በሰነድ ዝግጅቱ የተሳተፋ ባለሙያዎች፣ የሄግ ድርጅት ተወካዮች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላትና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

በመድረኩ የፍትህ ሚኒስቴር የተቋም ግንባታና ሪፎርም ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ኤርሚያስ የማነብርሃን (ዶ/ር )÷ የኢትዮጵያ የመሬት ፍትህ አመላካቸ ሰነድ ለፖሊሲና በዘርፉ ለሚኖረው ፍትሕ አሰጣጥ አጋዥ ሊሆኑ የሚችሉ ልምዶችና ተሞክሮዎችን የያዘና ተግባራዊ ሊደረጉ የሚችሉ ሂደቶችን ያካተተ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

የሄግ ኢኖቬሽን የህግ ተቋም ዋና ስራ አስፈፃሚ ሳሙኤል ሙለር (ዶ/ር)በበኩላቸው÷ ሰነዱ በመሬት ላይ የሚነሱ አለመግባባቶችን ለመፍታት የሚያስችሉና በመሬት ፍትህ አስተዳደር ውስጥ ያሉ ተዋንያን ሊጠቀሙበት የሚችሉበት እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

ሰነዱ ከባህላዊና መደበኛ የግጭት መፍቻ ዘዴዎች ውስጥ ልምዶችን በመውሰድና በማቀናጀት የኢትየጵያ የመሬት ፍትህ ለሁሉም ፍትሀዊ፣ዘላቂ እና ተደራሽ እንዲሆን ለማድረግ ያለመ መሆኑ መገለጹን የፍትህ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

በተያያዘም ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ ስራ ላይ የዋለው የኦሮሚያ ባህል ፍርድ ቤቶች አዋጅን አስመልክቶ የህግ አፈፃፀም የተፅዕኖ ግምገማ ጥናት ሪፖርት ቀርቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.