የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) 15ኛው የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ የመክፈቻ ስነ ስርዓት በአፍሪካ ህብረት እየተካሄደ ይገኛል።
በመክፈቻ ስነ ስርዓቱ ላይ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴን ጨምሮ የአባል ሀገራት ሚኒስትሮች ተገኝተዋል።
ስብሰባው ለሁለት ቀናት የሚካሄድ ሲሆን አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት ተፈርሞ ወደ ስራ ከተገባ በኋላ የተከናወኑ ተግባት ሪፖርቶች ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
እንዲሁም የመግባቢያ ስምምነት በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ዋና ፀሃፊ ዋምኬሌ ሜኔ እና በፓን አፍሪካ የጥራት መሠረተ ልማት ተቋማት ሊቀመንበር ሄንሪ ሮቲች (ዶ/ር) መካከል እንደሚፈረም ተጠቁሟል።
ኢትዮጵያን ጨምሮ 54 የአፍሪካ ሀገራት ስምምነት የፈረሙበት የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና አንድ የአፍሪካ ገበያን በመፍጠር የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራትን ከ1 ነጥብ 3 ቢሊየን በላይ ህዝብን ያስተሳስራል ተብሎ ይጠበቃል።
በነፃ የንግድ ቀጣና ትስስሩ 3 ነጥብ 4 ትሪሊየን ዶላር ግብይት እንደሚፈጠርም ይጠበቃል።
በታሪኩ ለገሰ