Fana: At a Speed of Life!

ስምምነቱን ተከትሎ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባላት ወደ ካምፕ መግባት ጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 24፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል መንግሥት እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አመራሮች የደረሱትን የሰላም ስምምነት ተከትሎ የሠራዊቱ አባላት ወደ ተዘጋጀላቸው ካምፕ መግባት ጀምረዋል፡፡

ሕዝብን ለስቃይ ሲዳርግ የነበረውን ችግር በሰላማዊ መንገድ የፖለቲካ ልዩነትንም በውይይት መፍታት ተገቢ መሆኑ ታምኖበት ባሳለፍነው እሁድ የሰላም ስምምነቱ መፈረሙ ይታወሳል፡፡

በዚሁ መሠረት በተለያዩ አካባቢዎች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባላት ወደ ተዘጋጀላቸው ካምፕ እየገቡ መሆኑን በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

የሠራዊቱ አባላት ወደ ካምፕ መግባታቸውም ስምምነቱ ወደ ተግባር መሸጋገሩን አመላካች ነው ተብሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.