Fana: At a Speed of Life!

ለሀገራዊ ምክክሩ ስኬት አባ ገዳዎችና ሃዳ ሲንቄዎች የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሀገራዊ ምክክሩን የተሳካ ለማድረግ አባ ገዳዎችና የሃዳ ሲንቄዎች ሚና ከፍተኛ መሆኑን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር መሐሙድ ድሪር ገለጹ።

ኮሚሽኑ ከኦሮሚያ ክልል ከተወጣጡ አባገዳዎችና ሃደ ሲንቄዎች ጋር ቀጣይ በክልሉ አጀንዳ የማሰባሰብ ሂደቱን የተሳካ ለማድረግ በሚቻልበት ሂደት ላይ በአዳማ እየመከረ ይገኛል።

ኮሚሽነር አምባሳደር መሐሙድ ድሪር በመድረኩ መክፈቻ ላይ እንደገለጹት÷በሀገሪቷ የነበሩና አሁንም የሚስተዋሉ ያለመግባባት ችግሮችን በምክክር እንዲፈቱ ኮሚሽኑ የማመቻቸት ስራዎችን እያከናወነ ነው።

በተለይም ባለፉት ጊዜያት የኮሚሽኑን ዓላማና ተልዕኮ ለህዝብ የማስገንዘብና የአጀንዳ ልየታ ስራዎች በአብዛኛው ክልሎችና በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች መከናወኑን አስታውሰዋል።

በአሁኑ ወቅትም በኦሮሚያ ክልል ከ7 ሺህ በላይ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ያሳተፈ የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ታህሳስ 7 ቀን 2017ዓ.ም ጀምሮ ለማከናወን ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል።

መድረኩ ህብረተሰቡ ችግሮች በምክክሩ ለመፍታት እየተደረገ ያለውን ጥረት ለማሳካት ወካይ አጀንዳዎችን እንዲያቀርብ ለማስቻል አባ ገዳዎችና ሃደ ሲንቄዎች ህዝቡን በማንቃትና በማስገንዘብ የድርሻቸውን እንዲወጡ ለማስቻል ያለመ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በተለይም ተባባሪ አካላትን በመምረጥና የአጀንዳ ልየታ ስራን የተሳካ በማድረግ ረገድ ህዝቡን በማስተባበር አባ ገዳዎች እና ሃደ ሲንቄዎች የሚኖራቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.