የባህርዳር ከተማ የሌማት ትሩፋት አመርቂ ውጤት አምጥቷል
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የባህርዳር ከተማ የሌማት ትሩፋት አመርቂ ውጤት ማሳየቱን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል የባሕርዳር ከተማ የሌማት ትሩፋት ማዕከል እንድትሆን የሚያስችሉ ተግባሮች እየተከናወኑ መሆኑን ተመልክተዋል።
ሚኒስትሩ የባሕርዳር ከተማ የሌማት ትሩፋት ውስጥ የተካተቱትን በተለይም በእንስሳት ተዋፅኦ ምርቶች ፣በማር ፣በዶሮና እንቁላል እንዲሁም በአሳ ሀብት ልማትና በአትክልትና ፍራፍሬ የተሰሩ ስራዎችን ተመልክተዋል።
ከጉብኝታቸው በኋላም ሚኒስትሩ በሌማት ትሩፋት ስራዎች ላይ እምርታዊ ለውጥ እየተመዘገበ እንደሚገኝ መግለጻቸውን ከአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ አመላክቷል።