በድሬዳዋ የመደመር ትውልድ ቤተ-መፃህፍት ግንባታ 50 በመቶ ደረሰ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በድሬዳዋ ከተማ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢንሼቲቭ እየተገነባ ያለዉ የመደመር ትውልድ ቤተ-መፃህፍት ግንባታ 50 በመቶ መድረሱ ተገለፀ።
ቤተ መፃህፍቱ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተፃፈው የመደመር ትውልድ መፅሃፍ ሽያጭ ገቢ እየተገነባ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
በባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ የተመራ ልዑክ የቤተ መፃፍቱን የግንባታ ሂደት የጎበኘ ሲሆን÷ በዚህ ወቅት የግንባታው 50 በመቶ መጠናቀቁ መገለፁን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
ቤተ-መፃህፍቱ ሰፊ የመኪና ማቆሚያ፣ የመፃህፍት መደብርና መሸጫ፣ ካፌና ሬስቶራንት ማካተቱ ታውቋል፡፡