Fana: At a Speed of Life!

 ብሔራዊ ቤተ-መንግሥት የዛሬ ልማትና ብልፅግና ማሳያ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ብሔራዊ ቤተ-መንግሥት የዛሬ ልማትና ብልፅግና ማሳያ ነው ሲሉ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ አቶ አክሊሉ ታደሰ ገለፁ፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት፣ የአንድነት ፓርክ አስተዳደር እና የብሔራዊ ቤተመንግስት አስተዳደር ሰራተኞች እድሳት የተደረገለትን የብሔራዊ ቤተ-መንግስት ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ አቶ አክሊሉ÷ የብሔራዊ ቤተ-መንግሥት የትናንት ታሪካችን ሰነድ፣ የዛሬ ልማትና ብልፅግና ማሳያ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ጎብኝዎቹ በበኩላቸው ብሔራዊ ቤተ መንግስት በተደረገለት ዕድሳትና ባዩት ለውጥ መደሰታቸውን ገልፀዋል፡፡

በለይኩን ዓለም

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.