በጅማ ከተማ የከተራ በዓል እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጅማ ከተማ የከተራ በዓል በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ ነው፡፡
በአከባበሩ ላይ የጅማ፣ የየም እና የሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጽኡ አቡነ እስጢፋኖስን ጨምሮ ካኅናት እና ሕዝበ ክርስቲያኑ ተገኝተዋል፡፡
ከከተማው 16 ደብሮች የተውጣጡ ታቦታት ከመንበራቸው ወጥተው ወደ ጥምቀተ ባሕሩ እያመሩ ነው።
በወርቃፈራው ያለው እና ተስፋሁን ከበደ