የከተራ በዓል በሀዋሳ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጥምቀት ከተራ በዓል በሀዋሳ ከተማ በደመቀ መልኩ እየተከበረ ነው።
ታቦታት ከመንበረ ክብራቸው ወጥተው ጉዞ በማድረግ ላይ ሲሆኑ የመስቀለ ኢየሱስ ታቦትም በሀይቁ ላይ በጀልባ ታጅቦ በሀይቁ ዳርቻ ወደሚገኘው ጥምቀተ ባህር በበማቅናት ላይ ይገኛል።
በርካታ ምዕመናን እና የበዓሉ ታዳሚያዎችም ታቦታትን አጅበው በመጓዝ ላይ ናቸው።
በብርሃኑ በጋሻው እና ነገሆ ብዙነህ