ጥምቀትን በጎንደር ለመታደም የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች ጎንደር እየገቡ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቱሪዝም ሚንስትር ሰላማዊት ካሰ ጥምቀት በዓልን ለመታደም ጎንደር ከተማ ገብተዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ፣ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር እና የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደን ጨምሮ የፌደራል እና የክልል አመራሮች የጥምቀት በዓልን ለመታደም ቀደም ብለው ጎንደር ከተማ መግባታቸው ይታወቃል፡፡
ጎንደር ከተማ ጥምቀት በዓል በልዩ ድምቀት ከሚከበርባቸው ከተሞች መካከል አንዷ መሆኗ ይታወቃል፡፡
በምናለ አየነው