የጎንደርን ሰላም አጽንታችሁ ጠብቁ – ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ
አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጎንደርን ሰላም አጽንታችሁ ጠብቁ ሲሉ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ አስገነዘቡ።
በአፄ ፋሲለደስ ባህረ ጥምቀት እየተከናወነ በሚገኘው የጥምቀት በዓል ሥነ-ሥርዓት ላይ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ፣ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘው ተሻገር፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግስሥት የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ፕሬዚዳንት ታዬ ባስተላለፉት መልዕክት፤ የሰላም ዋጋው ውድ ነው የጎንደርን ሰላም አፅንታችሁ ጠብቁ ሲሉ አሳስበዋል።
ጎንደር የዕውቀትና የጥበብ መናኸሪያ ናት ያሉት ፕሬዘዳንቱ፤ የቀደመውን ሀብት ጠብቀው ያቆዩ ሁሉ ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።
የአሁኑ ትውልድ የአባቶቹን ፈለግ ተከትሎ ታሪክ ማስቀጠል እንዳለበትም አስገንዝበዋል።
በምናለ አየነው