የጃፓን ዲቨሎፕመንት ኢንስቲትዩት ኢትዮጵያ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችን ለማልማት አመቺ መሆኗን ገለጸ
አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጃፓን ዲቨሎፕመንት ኢንስቲትዩት በተለያዩ ሀገራት ያለውን የልዩ ኢኮኖሚ ዞን አስተዳደር እና ልማት ልምድ እንዲተገብር በትኩረት እንደሚሰራ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ዋና ስራ አስፈጻሚው የጃፓን ዲቨሎፕመንት ኢንስቲትዩት ፕሬዚዳንት ሾይቺ ካባያሽን (ዶ/ር) ጋር ባደረጉት ውይይት÷ ኮርፖሬሽኑ በሚያስታዳድራቸው ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ያለውን የኢንቨስትመንት ፍሰት ለማሳደግ ከኢንስቲትዩቱ ጋር በትብብር መስራት አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
ለዚህም አስፈላጊው ትብብር ይደረጋል ማለታቸውን የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡
ሾይቺ ካባያሽን (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ በዘርፉ ያላት እምቅ አቅም በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችን ለማልማት አመቺ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ለዚህም ኢንስቲትዩቱ በተለያዩ ሀገራት ያለውን የማማከር ልምድ ለመተግበር እንደሚሰዋ አረጋግጠዋል።
የጃፓን ዲቨሎፕመንት ኢንስቲትዩት ከ75 በላይ በሚሆኑ ሀገራት ከ350 በላይ ፕሮጀክቶችን በማማከርና ወደ ትግበራ በማስገባት ከ40 ዓመታት በላይ ልምድ ያለው ኩባንያ ነው ተብሏል፡፡