Fana: At a Speed of Life!

የኔዘርላንድስ ባለሀብቶች በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ የተፈጠሩ ዕድሎችን እንዲጠቀሙ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከኔዘርላንድስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ስቲጅን ጃንሰን ጋር ተወያይተዋል።

 

ውይይቱ በሁለትዮሽ ትብብር፣ በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል።

 

አምባሳደር ምስጋኑ በውይይቱ ወቅት÷ የኔዘርላንድስ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት እያደረጉት ካለው ተሳትፎ በተጨማሪ በመተግበር ላይ ባለው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ የተፈጠሩ ዕድሎችን በስፋት እንዲጠቀሙ ጥሪ አቅርበዋል።

 

ልዩ መልዕክተኛዋ ስቲጅን ጃንሰን በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ በቀጣናው ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን የምታደርገውን ጥረት አድንቀው ኔዘርላንድስ ድጋፍ እንደምታደርግ ማረጋገጣቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።

 

 

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.