Fana: At a Speed of Life!

ሔር ኢሴ ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሶማሌ ዒሳ ማህበረሰብ ያልተጻፈ ባሕላዊ ሕግ “ሔር ኢሴ” ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት በድሬዳዋ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

በውይይት መድረኩ የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳን ጨምሮ የሶማሊያ እና የጅቡቲ ባህልና ቱሪዝም የሥራ ሃላፊዎች እና ሌሎች እንግዶች ተሳትፈዋል፡፡

የፓናል ውይይቱ በሔር ኢሴ ላይ ለረጅም ዓመታት የተለያየ ጥናታዊ ጽሑፍ ባደረጉ ምሁራን ስለ ቅርሱ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ማብራሪያ ለማቅረብ ያለመ ነው ተብሏል፡፡

በመድረኩ ሔር ኢሴ የኢትዮጵያ፣ ሶማሊያና ጅቡቲን የሕዝብ ለሕዝብ ትስስር እና ወንድማማችነት ማጠናከር ላይ ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳለው ተነስቷል፡፡

ስለሆም ሔር ኢሴ የሀገራቱን ሕዝቦች አብሮነትና ወንድማማችነት እንዲያጠናከር በትብብር መስራት እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡

“ሔር ኢሴ” በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የሰው ልጆች ወካይ ዓለም አቀፍ የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ እንዲመዘገብ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት የምስጋና እና የእውቅና መርሐ ግብር በድሬዳዋ ከዛሬ ጀምሮ ይካሄዳል፡፡

የድሬዳዋ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሚካኤል እንዳለ መርሐ ግብርሩ በተለያዩ ሁነቶች የሚከበር መሆኑን ገልጸዋል።

የሔር ኢሴ ባህላዊ እሴትን የጋራ በማድረግ ለቱሪስት መስህብነት መጠቀምና ለቀጣይት ትውልድ እንዲተላለፍ ሁሉም ሃላፊነቱን እንዲወጣ መርሐ ግብሩ ሚና እንዳለው ጠቁመዋል።

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.