ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) በዳውሮ ዞን የተገነባውን የድንጋይ ከሰል ማጠቢያ ፋብሪካ መረቁ
አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ዳውሮ ዞን የተገነባውን የኢቲ ማዕድን ልማት አ.ማ የድንጋይ ከሰል ማጠቢያ ፋብሪካ መርቀው ሥራ አስጀምረዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷በዛሬው ዕለት በዳውሮ ዞን የተገነባውን የኢቲ ማዕድን ልማት አ.ማ የድንጋይ ከሰል ማጠቢያ ፋብሪካ መርቀን ስራ አስጀምረናል ብለዋል።
ፋብሪካው በሀገር አቀፍ ደረጃ ያለውን የድንጋይ ከሰል ምርት ከማሻሻል ባሻገር ለበርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች የስራ እድል እንደፈጠረም አስገንዝበዋል፡፡