Fana: At a Speed of Life!

ጠንካራ ሰራዊት ተገንብቷል- አይሻ መሀመድ(ኢ/ር)

 

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ለውጡን ተከትሎ ለሀገርና ለሕዝብ የወገነ በላቀ መልኩ ግዳጅ መፈፀም የሚችል ጠንካራ ሰራዊት ተገንብቷል ሲሉ የመከላከያ ሚኒስትሯ አይሻ መሀመድ (ኢ/ር) ገለጹ።

የመከላከያ ሚኒስትሯ፥ ተቋማዊ አቅምን ለመገንባት በተከናወኑ የለውጥ ሥራዎችና የተገኙ ውጤቶችን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

መከላከያ ሰራዊት ጠንካራ ተቋም እንዲሆን እንዲሁም ቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎችን ታሳቢ ያደረገ አደረጃጀት እንዲኖረው በርካታ የለውጥ ሥራዎች መከናወናቸውን አንስተዋል።

የሰራዊቱ አደረጃጀት ህብረ ብሄራዊነትን መሰረት ያደረገ፣ በቴክኖሎጂ የታገዘና የላቀ የመፈጸም ብቃትን የተላበሰ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

በመሆኑም ለሀገርና ለሕዝብ የወገነ በላቀ መልኩ ግዳጅ መፈፀም የሚችል ጠንካራ ሰራዊት መገንባቱን ሚኒስትሯ አረጋግጠዋል።

ሰራዊቱ በያለበት አካባቢ በልማትና በጎ አድራጎት ሥራዎች ላይ በመሳተፍ ህዝባዊነቱን በተግባር እያሳየ መሆኑንም ገልጸዋል።

ከጥናትና ምርምር አኳያም በሰራዊቱ ተቋማት ቴክኖሎጂዎችን ጨምሮ ችግር ፈቺ ምርምሮች ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሯ፥ ከዚህም ተጨባጭ ውጤቶች እየተገኙ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ከውጭ ግንኙነት አኳያ ከተለያዩ አገራት ጋር ሥምምነት በመፈራረም በስልጠና እና አቅም ግንባታ ስራዎች ላይ በትብብር እየተሰራ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

በተለይም የጎረቤት አገራትን ጨምሮ ከተለያዩ የአፍሪካ አገራት የሚመጡ የሰራዊት አመራሮችን ልምድና ተሞክሮ የማጋራት ስራ መከናወኑን አንስተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.