Fana: At a Speed of Life!

የአገው ፈረሰኞች ሰላምንና ጸጥታን በማስከበር ረገድ ሚና እየተጫወቱ ነው – ም/ጠ/ሚ ተመስገን

 

አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአገው ፈረሰኞች የአባቶቻቸውን ፈለግ በመከተል ሰላምንና ጸጥታን በማስከበር ረገድ ተገቢውን ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ተናገሩ፡፡

ም/ጠ/ሚ ተመስገን ለ85ኛው የአገው ፈረሰኞች ምስረታ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመልዕክታቸውም÷ የአገው ፈረሰኞች የኢትዮጵያን ዳር ድንበርና ሉዓላዊነት በማስጠበቅ ረገድ ታላቅ ሚና ነበራቸው፤ ለዚህም የዓድዋ ዘመቻ ተሳትፏቸው ጉልሕ ምስክር ነው ብለዋል።

ዛሬም የአባቶቻቸውን ፈለግ በመከተል ሰላምንና ጸጥታን በማስከበር ተገቢውን ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ ነው ያሉት፡፡

ዛሬ የሚከበረው በዓል “ፈረሰኞቻችንና ፈረሶቻችን የሰላምና የልማት ዘብ መሆናቸውን ለትውልድ የሚመሰክሩበት እንደሚሆን አምናለሁ”ሲሉም በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.