ርዕሰ መሥተዳድር ጥላሁን ለብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ
አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ጥላሁን ከበደ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ሆነው በድጋሚ መመረጣቸውን ተከትሎ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባዔ ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) የፓርቲው ፕሬዚዳንት አድርጎ መርጧል።
ይህንን ተከትሎም ርዕሰ መሥተዳድሩ ባስተላለፉት የመልካም ምኞት መልዕክት÷ ለፓርቲው ፕሬዚዳንት መልካም የሥራ ዘመን ተመኝተዋል።