Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክልል መንግስት የግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸም እየተገመገመ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኦሮሚያ ክልል መንግስት የ2017 በጀት ዓመት ያለፉት 6 ወራት ሥራ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

በመድረኩ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ግምገማው የክልሉ መንግስት ያለፉት ስድስት ወራት የመንግሥትና የፓርቲ አፋጻጸም ላይ አተኩሮ እንደሚካሄድ ተገልጿል።

በዚህም በግማሽ ዓመቱ በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ መስኮች የተመዘገቡ ስኬቶች፣ የተገኙ ተሞክሮዎችና የታዩ ክፍተቶች ላይ በጥልቀት በመወያየት ቀጣይ አቅጣጫ ይቀመጣል ተብሎ ይጠበቃል።

በራሃማ አህመድ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.