Fana: At a Speed of Life!

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ቁልፍ የኢኮኖሚ ችግሮችን መቅረፉ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በመንግስት ተግባራዊ የተደረገው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ቁልፍ የኢኮኖሚ ችግሮችን መቅረፉን የገንዘብ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት የ2017 በጀት ዓመት የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማ ተካሂዷል፡፡

በግምገማው የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሺዴ÷ ባላፋት ስድስት ወራት ተግባራዊ የተደረገው የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ውጤታማ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

በቀሪው ግማሽ አመት በታክስ ፖሊሲ አፈጻጸም፣ በውጭ ሀብት አሰባሰብ፣ በዕዳ ሽግሽግ የጋራ ማዕቀፍ አፈጻጸሞች፣ በጥሬ ገንዘብ ፍሰት ማኔጅመንትና በበጀት ዝግጅት ላይ ትኩረት ተሰጠቶ እንደሚሰራ ጠቁመዋል፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴር ዴኤታ  ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ ያለፉት ስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም በተናበበና በተቀናጀ ሁኔታ የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተግባራዊ ተደርጎ የኢኮኖሚ ማነቆ የነበሩ ችግሮች እልባት ያገኙበት ነበር ብለዋል፡፡

ውጤቱ ሊመዘገብ የቻለው አመራሩና ሰራተኛው ተቀናጅቶ በመስራቱ መሆኑን የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታው÷ ትብብሩና ቅንጅቱ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.