Fana: At a Speed of Life!

40 ሺህ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የንጹሕ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ተመረቁ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደብረ ብርሃን ከተማ ከ296 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነቡ የንጹሕ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል፡፡

ፕሮጀክቶቹ 40 ሺህ የከተማዋ ነዋሪዎችን የንጽሕ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚያስችሉ ተገልጿል፡፡

በዚህም የከተማውን የንጹሕ የመጠጥ ውሃ ተደራሽነት ከ51 በመቶ ወደ 74 በመቶ ማሳደግ መቻሉ ተጠቁሟል፡፡

ፕሮጀክቶቹ የአማራ ክልል ውሃና ኢነርጂ ቢሮ ሃላፊ ማማሩ አያሌው (ዶ/ር) በተገኙበት በዛሬው ዕለት ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል፡፡

በኤልያስ ሹምዬ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.