ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ከጋና እና ቡሩንዲ ፕሬዚዳንቶች ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከጋና ፕሬዚዳንት ጆን ማሀማ እና ከቡሩንዲ ፕሬዚዳንት ኤቫርሴት ንዳይሽሚዬ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም÷በአህገሪቱ ያሉ የልማት እድሎችንና ተግዳሮቶችን በተመለከተ ምክክር ማድረጋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡
ኢትዮጵያ እና ሀገራቱ በተለያዩ ዘርፎች ላይ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር ስምምነት ላይ መደረሱንም ተናግረዋል፡፡
የመሪዎቹ ውይይት ሁለተኛ ቀኑን በያዘው የአፍሪካ ኅብረት 38ኛ መደበኛ ጉባኤ ጎን ለጎን ነው የተካሄደው፡፡