ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ያሰለጠናቸውን 2 ሺህ 717 ተማሪዎች አስመረቀ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ወለጋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 2 ሺህ 717 ተማሪዎች በዛሬው ዕለት አስመርቋል፡፡
ተመራቂዎቹ በመደበኛና በተለያዩ መርሐ-ግብሮች በመጀመሪያ ዲግሪ፣ በ2ኛ ዲግሪና በ3ኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ የምስራቅ ወለጋ ዞን አመራሮች፣ የዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንትና የሴኔት አባላት እንዲሁም የተመራቂ ተማሪዎች ወላጆች ተገኝተዋል፡፡
በዮሃንሰ መልካሙ እና ገላን ተስፋ