Fana: At a Speed of Life!

የኢስዋቲኒ ንጉሥ ምስዋቲ ሣልሳዊ ብሔራዊ ቤተ-መንግሥትን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የኢስዋቲኒንጉሥ ምስዋቲ ሣልሳዊን ብሔራዊ ቤተ-መንግሥትን አስጎብኝተዋቸዋል።

ንጉሥ ምስዋቲ ሣልሳዊ በዚሁ ወቅት፥ በፕሬዚዳንቱ ግብዣ ብሔራዊ ቤተ መንግሥትን በመጎብኘታቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል።

ቤተ- መንግሥቱ  በርካታ ታሪኮችን በውስጡ የያዘ እንደሆነ መመልከታቸውንም አንስተዋል፡፡

ቀደምት አፍሪካውያን መሪዎች ለአፍሪካ አንድነት የመከሩበት የጋራ ማዕድ የቆረሱበት፣ በጥቅሉ የአፍሪካን እጣ ፈንታ የሚወስኑ ትልልቅ ውሳኔዎችን ያሳለፉበት መሆኑም ልዩ ያደርገዋል ነው ያሉት።

ይህም ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴን ጨምሮ የኢትዮጵያ መሪዎች ለአፍሪካ ያደረጉትን ጉልህ አስተዋፅኦ የሚዘክር እንደሆነ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.