Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና አልጀሪያ ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ እና አልጀሪያ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ።

በአልጀሪያ የኢትዮጵያ አምባሳደር በመሆን የተሾሙት ነቢያት ጌታቸው በኢትዮጵያ የአልጀሪያ አምሳደር እና የሀገሪቱ የአፍሪካ ህብረት ቋማ ተጠሪ ከሆኑት ኤልሃምዲ ሳላህ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም የሁለቱን ሀገራት ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መከረዋል።

እንዲሁም ሁለቱ ሀገራት በቀጣናዊ እና አለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ ትብብራቸውን ማጠናከር በሚችሉበት ዙሪያም ተወያይተዋል

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.