Fana: At a Speed of Life!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ወደ ብሔራዊ ባንክ በሚገባው የወርቅ ምርት ላይ መነቃቃት መታየቱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ ወደ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ወደ ብሔራዊ ባንክ በሚገባው የወርቅ ምርት ላይ ከፍተኛ መነቃቃት መታየቱን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ገለጹ፡፡

የክልሉ ምክር ቤት ጉባኤ ላይ ሪፖርት ያቀረቡት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ የክልሉ መንግስት የማዕድን ሀብቱ ለሀገር ኢኮኖሚ የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ የበለጠ ለማሳደግ የቅርብ ክትትልና ድጋፍ እያደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡

በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ አጋማሽ በልዩ አነስተኛና በባህላዊ ወርቅ አምራች እንዲሁም በኩባንያዎች 22 ነጥብ 2 ኩንታል ወርቅ ወደ ብሔራዊ ባንክ እንዲገባ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ በወርቅ መግዣ ላይ የተደረገዉ ከፍተኛ ጭማሪና ማበረታቻ በህገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረዉን የወርቅ መጠን እንዲቀንስ ማድረጉን ገልጸዋል።

ይህም ወደብሔራዊ ባንክ የሚገባው የወርቅ ምርት በከፍተኛ ሁኔታ እንዲነቃቃ አድርጓል ነው ያሉት፡፡

በተጨማሪም ባለፉት ስድስት ወራት 948 ሜትሪክ ኪዩብ እምነበረድ እና 34 ሺህ 253 ቶን የድንጋይ ከሠል መመረቱን ርዕሰ መስተዳድሩ መናገራቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.