Fana: At a Speed of Life!

95 መደበኛ ያልሆኑ ፍልሰተኞች ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 95 መደበኛ ያልሆኑ ፍልሰተኞች በባቡር ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ መደረጉን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ፡፡

ዜጎቹ ወደ ሀገራቸው የተመለሱት ጅቡቲ ከሚገኘው የዓለም አቀፍ ፍልሰተኞች ድርጅት ጋር በመተባበር መሆኑ ተገልጿል፡፡

ህገ-ወጥ የስደት መንገድ እጅግ አደገኛ እና ዜጎችን ከህግ ከለላ ውጪ ለበርካታ የአካል እና የስነ-ልቦና ጉዳት እየዳረገ ያለ በመሆኑ ሁሉም ዜጋ ራሱን እና ቤተሰቡን ከዚህ አደጋ መጠበቅ እንደሚገባው የኤምባሲው መረጃ አስገንዝቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.