ኅብረቱ ከስደት ተመላሾችን ለማቋቋም ድጋፌን እቀጥላለሁ አለ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 11 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአውሮፓ ኅብረት ከስደት ተመላሾችን በዘላቂነት ለማቋቋም በሚደረገው ጥረት ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ፡፡
የካርቱም ፕሮሰስ አካል የሆነ ከስደት ተመላሾችን በዘላቂነት መልሶ ማቋቋም ላይ ያተኮረ መድረክ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
በዚሁ ወቅት ስደትን በተመለከተ ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት በባለድርሻ አካላት መካከል ምክክር ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ አስገንዝበዋል፡፡
በተለይም የፍልሰት መነሻና መዳረሻ እንዲሁም ድንበር የሚጋሩ ሀገራት በትብብር መሥራት እንደሚጠበቅባቸው አስረድተዋል፡፡
በአውሮፓ ኅብረት ኮሚሽን የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ባለሙያ ሮበርት ሪቢ በበኩላቸው ÷ ከስደት ተመላሾችን በዘላቂነት ለማቋቋም በሚደረገው ጥረት ኅብረቱ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
ከስደት ተመላሾች በዘላቂነት እዲቋቋሙም በቂ የሥራ ዕድሎችን ማቅረብ እና በኢንቨስትመንት የሚሰማሩበትን ሁኔታ ማመቻቸት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
በመሳፍንት ብርሌ