የሴቶች ብሔራዊ ቡድኑ ካምፓላ ገባ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ኡጋንዳ ካምፓላ ገብቷል።
ብሔራዊ ቡድኑ ኢንተቤ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ በዩጋንዳ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተወካዮች እንዲሁም የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ በዩጋንዳ አባላት አቀባበል አድርገውለታል፡፡
ሉሲዎቹ ማረፊያቸውን በኢንተቤ በሚገነው ሂልተን ጋርድን ሂል ያደረጉ ሲሆን 11 ሰዓት ጀምሮ መጀመሪያ ልምዳቸውን ያደርጋል መባሉን ከፌዴሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡