Fana: At a Speed of Life!

ገዢ ትርክቶችን ከማስረጽ ረገድ ውጤታማ የሕዝብ ግንኙነት ሥራ ተከናውኗል – ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ወንድማማችነትንና እህትማማችነትን የሚገነቡ ገዢ ትርክቶች እንዲሰርጹ በማድረግ ውጤታማ የሕዝብ ግንኙነት ሥራ መከናወኑን የብልጽግና ፓርቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) ገለፁ።

የብልጽግና ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ የ2017 በጀት ዓመት የ6 ወራት የሥራ አፈጻጸም የግምገማ መድረክ በሰመራ ከተማ እየተካሄደ ነው።

ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት÷በኢትዮጵያውያን መካከል ወንድማማችነትንና እህትማማችነትን የሚገነቡ ትርክቶች እንዲሰርፁ በማድረግ ረገድ ውጤታማ የሕዝብ ግንኙነት ሥራ ተከናውኗል ብለዋል።

የብልጽግና ፓርቲ እሳቤዎች ለሕዝብና ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ በማስተዋወቅ በኩልም ውጤታማ የተግባቦት ሥራ መከናወኑን አንስተዋል።

የዴሞክራሲ ባህል እንዲሰፍን፣ የልማት ሥራዎች እንዲሳኩ፣ አዎንታዊና ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን፣ የዓለም አቀፍ ግንኙነት በመርሕ ላይ እንዲመሰረት በዘርፉ የተሰሩ የሚዲያና የተግባቦት ሥራዎች አመርቂ ውጤት ማስመዝገባቸውን አስረድተዋል።

ለሁለት ቀን በሚቆየው የግምገማ መድረክ የሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የፓርቲው ሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ሃላፊዎች መሳተፋቸውን የፓርቲው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.