ከ658 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ መግባቱ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ለ2017/18 የምርት ዘመን ግብዓት የሚሆን ከ700 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ የአፈር ማዳበሪያ ጅቡቲ ወደብ መድረሱን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ለምርት ዘመኑ 2 ነጥብ 4 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ገዝቶ ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ከተያዘው እቅድ ውስጥ እስከ የካቲት 23 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ 700 ሺህ 763 በላይ ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ጅቡቲ ወደብ መድረሱ ተጠቁሟል፡፡
ጅቡቲ ወደብ ከደረሰው የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ 658 ሺህ 249 በላይ ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ተጓጉዞ ወደ ሀገር ውስጥ መግባቱን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
ወደ ሀገር ውስጥ ከተጓጓዘው ውስጥ 418 ሺህ 670 በላይ ሜትሪክ ቶን ዳፕ እንዲሁም 239 ሺህ 579 ሜትሪክ ቶን ዩሪያ የተሰኘው የአፈር ማዳበሪያ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡