Fana: At a Speed of Life!

ለትግራይ ክልል የ60 ሚሊየን ብር የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ለትግራይ ክልል ከ60 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል፡፡

ድጋፉ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ጽ/ቤት ኃላፊ ዑስታዝ አቡበከር አሕመድ አስተባባሪነት ከኦርፋንስ ኢንኒድዩኤስኤ የተበረከተ ነው ተብሏል፡፡

የተደረገው ድጋፍ የመለስተኛ ቀዶ ሕክምና እና ሌሎች አስፈላጊ ግብዓቶችን ያካተተ መሆኑን የምክር ቤቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ አማኑዔል ሃይለ ለተደረገው የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.