የኮንክሪት ሩፍ ታይልስ ፋብሪካ የሙከራ ምርት ማምረት ጀመረ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የኮንክሪት ሩፍ ታይልስ ማምረቻ ፋብሪካ የሙከራ ምርት ማምረት ጀምሯል፡፡
ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ ወደ ሥራ ሲገባ በቀን እስከ 2 ሺህ 500 ሩፍ ታይሎችን ማምረት እንደሚችል ተገልጿል፡፡
የኮንክሪት ሩፍ ታይልስ ማምረቻ ፋብሪካ ቃሊቲ በሚገኘው የኢንዱስትሪ መንደር የተተከለ መሆኑን የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡