ግሎባል ቫይታል ስትራቴጅ ለአገልግሎቱ የሚያደርገውን ድጋፍ እንደሚያስቀጥል አረጋገጠ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት ከግሎባል ቫይታል ስትራቴጅ ፕሬዚዳንት እና ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሜሪ አን (ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል፡፡
በዚሁ ወቅት ዋና ዳይሬክተሯ፤ በሲቪልና በቤተሰብ ምዝገባ ዙሪያ ተቋሙ ከዚህ በፊት የሠራውን ሥራና በቀጣይ ዲጅታላይዝ ከማድረግ አኳያ እያከናወናቸው ያሉ ተግባራትን አብራርተዋል፡፡
እስከ አሁን ለተደረገው ድጋፍ አመሥግነው፤ በቀጣይ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተመሳሳይና ወጥ የሆነ የአሠራር ሥርዓት ለመገንባት ድጋፍ እንዲደረግ ጠይቀዋል፡፡
ሜሪ አን (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የሲቪልና የቤተሰብ ምዝገባን ከጤና ዘርፍ ጋር በተቀናጀ መልኩ መሥራት ጠቀሜታ እንዳለው ማስገንዘባቸውን የአገልግሎቱ መረጃ አመላክቷል፡፡
በዘርፉ ከዚህ በፊት የተለያዩ ድጋፎች ሲደረጉ መቆየታቸውን አውስተው፤ በቀጣይም ድጋፍ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል፡፡