የኢትዮጵያ ሴቶች ለሀገራቸው ነፃነት የላቀ አስተዋጽዖ አበርክተዋል- ፕሬዚዳንት ታዬ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሴቶች ለሀገራቸው ነፃነት እና የኢኮኖሚ ዕድገት የላቀ አስተዋጽዖ ማበርከታቸውን ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ገለጹ፡፡
ፕሬዚዳንቱ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው፤ ለዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን የእንኳን አደረሳችሁ የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በመልዕክታቸውም፤ የኢትዮጵያ ሴቶች ለሀገራቸው ነፃነት፣ የኢኮኖሚ ዕድገት፣ ማኅበራዊ እሴቶችና ባህሎችን ለማፅናት ያበረከቱት አስተዋፅዖ የላቀ ነው ብለዋል።
እንቅፋቶችንና ጎታች እሳቤዎችን በመጣል፣ በመላ አቅማቸው የሀገራችን የመዘመን መንገድ ዋነኛ መሪና ተዋናይ መሆናቸው እሙን ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡