የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ጅግጅጋ ገቡ
የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ጅግጅጋ ገቡ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ገብተዋል፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ ጅግጅጋ ከተማ ሲገቡ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
አቶ አወል በዛሬው ዕለት በጅግጅጋ የሶማሌ እና አፋር ወንድም ህዝብ በጋራ የሚያፈጥሩበት ኢፍጣር ለአብሮነትና ለሰላም መርሐ ግብር ላይ ይታደማሉ፡፡
በመርሐ ግብሩ የሃይማኖት አባቶች፣ የሃገር ሽማግሌዎች እና የፌደራል መንግስት ተቋማት ሃላፊዎች እንደሚገኙም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡