Fana: At a Speed of Life!

የበልግ አብቃይ አካባቢዎች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ ተባለ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የበልግ አብቃይ አካባቢዎች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ ሲል የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡

በሚቀጥሉት አሥር ቀናት ለዝናብ መፈጠር አስተዋጽኦ የሚያደርጉ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች እንደሚጠናከሩ የትንበያ መረጃዎቹ አመላክተዋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘም በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በመካከለኛው፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ እንዲሁም በስምጥ ሸለቆና አጎራባች አካባቢዎች የተሻለ ጥንካሬ ይኖራቸዋል ብሏል፡፡

ከሚጠናከሩት የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ላይ በመነሳት የበልግ አብቃይ አካባቢዎች በርካታ ቦታዎቻቸውን የሚሸፍን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ።

አካባቢዎቹ በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ደግሞ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ ሲል የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ጠቁሟል።

በተጨማሪም ከሚኖረው ከፍተኛ የፀሐይ ሀይል ጋር በተያያዘ በተለይም በጋምቤላ፣ በአፋር፣ በሶማሌ፣ በቤንሻንጉል-ጉሙዝና በምዕራብ አማራ አካባቢዎች ላይ የቀኑ ከፍተኛ ሙቀት ከ35 እንዲሁም በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ከ40 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆን ተመላክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.